የጉዳት ዳረጎት አበል ጥያቄ ሲቀርብ መሟላት ያለባቸዉ ማስረጃዎች

1. መጀመሪያ ሲቀጠሩ /ስራ ሲጀምሩ/ የሞሉት የህይወት ታሪክ ፎርም የመጀመሪያው እንዳልተገኘ ከተገለጸ ቀጥሎ የተሞላ የህይወት ታሪክ ፎርም ( ከአንድ በላይ መስሪያ ቤት አገልግሎት ለፈጸሙ).ያስሞሉት የህይወት ታሪክ ፎርም ከሌለ የለም የሚል ደብዳቤ ይጻፍ

2. የቅጥርና የስንብት ደብዳቤ (ከ – እስከ ተብሎ በአድራሻችን የተገለጸ)፣ ከአንድ በላይ ከሆነ ከእያንዳንዱ መስሪያ ቤት በአድራሻችን መጻፍ አለበት፡፡

3. የመንግስት አገልግሎት ሲያያዝ ካገለገሉበት መ/ቤት የተሰጣቸው የጡረታ መለያ ቁጥር መኖር አለመኖሩ መገለፅ አለበት

4. የአገልግሎት ጡረታ፣ ዳረጎት ወይም የጡረታ መዋጮ ተመላሽ መዉሰድ አለመዉሰዳቸዉ መገለፅ አለበት

5. የመንግስት አገልግሎት ከሌላቸው የግል ድርጅቱ ምንም አይነት የመንግስት አገልግሎት ስላለመፈፀማቸው በደብዳቤ መግለፅ አለበት

6. ጡረተኛ ከሆኑ የጡረታ ደብተራቸው ኮፒ መያያዝ አለበት

7. የደመወዝ ጭማሪ የተደረገበት ደብዳቤ መያያዝ አለበት

8. የሰራተኛው ሁለት ፎቶ ግራፍ ከጀርባዉ የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት

9. 37ኛው የወር ደመወዝ መሸኛ ላይ መገለፅ አለበት

10. የድርጅቱ መዋቅራዊ አደረጃጀትና የተጠና የደመወዝ ስኬል መላክ ይኖርበታል፡፡ ( ከዚህ በፊት ከተላከ መላኩ ይገለፅ )

11. የጋብቻ ማስረጃ ካለ ይያያዝ ከሌለ ስላለመኖሩ በባለመብቱ ይገለፅ

12. ሁሉም ኮፒ ማስረጃዎች ላይ የድርጅቱ ማህተም መደረግ ይኖርበታል

13. የጉዳት ማሳወቂያ ቅጽ ግ/ድ/ጡ/1.3 ተሞልቶ መቅረብ አለበት

14. እንደየሁኔታው የፖሊስ ሪፖርት(የመኪና አደጋ ሲሆን)

15. በህክምና ቦርድ የተረጋገጠ የህክምና የጉዳት መጠን ማስረጃ