- ለዐቅድ አባልነት ምዝገባ መቅረብ ያለባቸዉ ማስረጃዎች እና የሚጠበቁ ግዴታዎች
- የግል ድርጅትን ለማስመዝገብ መሟላት ያለባቸዉ ማስረጃዎች
- ለP.L.C /ኃላ/የተ/የግል ማ/፣ የሽርክና ማኅበር ወይም ለ Share Company ንግድ ምዝገባ/ ፈቃድ፣ የመመስረቻ ጽሁፍ፤ መተዳደሪያ ደንብ ፣የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት ፣ ፎቶ ኮፒ በሁሉም ማስረጃ ላይ ማህተም ተደርጎበት በሸኚ ደብዳቤና ከግል ድርጅቱ መመዝገቢያ ቅጽ ጋር የሠራተኞችን መመዝገቢያ ቅጽ በሶፍት ኮፒ ለመውሰድ ባዶ ሲዲ አብሮ መቅረብ አለበት፡፡
- P.L.C ላልሆኑ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ ሰርቲፊኬት ፎቶ ኮፒ ተደርጎ በሁሉም ማስረጃ ማህተም ተደርጎበት በሸኚ ደብዳቤ ከድርጅቱ መመዝገቢያ ቅጽ ጋር የሠራተኞችን መመዝገቢያ ቅጽ በሶፍት ኮፒ ለመውሰድ ባዶ ሲዲ አብሮ መቅረብ አለበት፡፡
- ለNGO የግብር ከፋይ ሰርቲፊኬት፣ የምዝገባ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ በሁሉም ማስረጃ ማህተም ተደርጎበት በሸኚ ደብዳቤ ከድርጅቱ መመዝገቢያ ቅጽ ጋር የሠራተኞችን መመዝገቢያ ቅጽ በሶፍት ኮፒ ለመውሰድ ባዶ ሲዲ አብሮ መቅረብ አለበት፡፡
ማሳሰቢያ፡- ማንኛውም ይህንን ፎርም ይዞ የሚመጣ ሰው የመ/ቤቱን ውክልና መያዝ አለበት፡፡
1.2 ሠራተኛ ለማስመዝገብ መሟላት ያለባቸዉ ማስረጃዎች
- ቅጽ ግድጡ1 በ2 ኮፒ ተሰርቶ ዋናው ወደ አስተዳደሩ ይመጣል፡፡ ቀሪው በአሠሪ ድርጅቱ የሠራተኛው ማህደር ውስጥ ይቀመጣል፡፡
- በድርጅቱ ሲቀጠሩ የተሰጣቸው ደመወዝ የሚገልጽ የቅጥር ደብዳቤ በተጨማሪም የደመወዝ ጭማሪ የተደረገባቸዉ ደብዳቤዎች፤
- የህይወት ታሪክ ፎርም (በድርጅቱ የተሞላ ካለ)ይቀርባል፤የህይወት ታሪክ ፎርም ከሌለ ደግሞ ”የለም” ተብሎ በደብዳቤ ይገለጻል፡፡
- የሠራተኛው ሁለት ፎቶ ግራፍ አንደኛው ከጀርባው አንደኛው ከፊት ለፊት ማህተም የተደረገበት፤
- ቀድሞ በመንግስት መ/ቤት ወይም በጡረታ ዐቅድ በተሸፈነ የግል ድርጅት ካገለገሉ ካገለገሉበት መ/ቤት የቅጥር፣ የህይወት ታሪክ ፎርም፣ የጡረታ መለያ ቁጥር እና የስንብት ደብዳቤ አገልግሎት ከ – እስከ ተገልፆ በድርጅቱ አድራሻ ተፅፎ መቅረብ አለበት፡፡
- የሚስት/የባል አንድ ፎቶ ግራፍ የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት ይያያዛል፡፡
- የጋብቻ ማስረጃ ተያይዞ ይቀርባል/ጋብቻ ካለ/
- ዕድሜያቸዉ ከ 18 ዓመት በታች የሆነ የልጆች የልደት ሠርቲፊኬት ይቀርባል፡፡
- ቅጽ ግድ ጡ1.1 (የምዝገባ ማሳወቂያ ቅፅ) ፎርሙን ለሞሉ ሠራተኞች ስም ዝርዝር በሁለት ኮፒ ተሠርቶ ይቀርባል፡፡
1.3 መረጃ የመስጠትና የመተባበር ግዴታ
- ማንኛውም የግል ድርጅትበአስተዳደሩ በሚተላለፈው መመሪያ መሰረት ለአዋጅ 1268/2014 አፈፃፀም የሚያስፈልጉ እያንዳንዱን የግል ድርጅት ሠራተኛ የሚመለከቱ መረጃዎችና ማስረጃዎች ማሰባሰብ፣ማጠናከር፣ማደራጀትና በአስተዳደሩ በሚወሰነው ጊዜና ቅፅ መሰረት ለአስተዳደሩ የማስተላለፍ ግዴታ አለበት፡፡
- በአዋጅ 1268/2014 አንቀፅ 53 ንዑስ አንቀፅ 2 መሰረት ማንኛውም ሰው የፅሁፍ ማስረጃእንዲልክ ወይም ቀርቦ አስተያየትና መረጃ እንዲሰጥ በአስተዳደሩ ሲጠየቅ የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡
- የሠራተኛ ማስረጃ አደራጅቶ የማይዝና በወቅቱ ለአስተዳደሩ የማያስተላልፍ የግል ድርጅት የሚመለከተዉ ኃላፊ በአዋጅ 1268/2014 አንቀጽ ፷፩ መሠረት ይቀጣል፡፡
1.4 የምዝገባ መረጃ ለውጥ ስለማሳወቅ
- ማንኛዉም የግል ድርጅት የራሱንና የግል ድርጅት ሰራተኛዉን የምዝገባ መረጃ የሚመለከት ለዉጥ ሲያጋጥም ለዉጡ በተከሰተ በ60 ቀናት ዉስጥ የተከሰተዉን ለዉጥ ከደጋፊ ማስረጃ ጋር አያይዞ ለአስተዳደሩ ማሳወቅ አለበት::
- እያንዳንዱ የግል ድርጅት ሰራተኛ የተተኪ ሁኔታን የሚመለከት የመረጃ ለዉጥ ሲያጋጥመዉ ከደጋፊ ማስረጃ ጋር ለሚሰራበት የግል ድርጅት በማቅረብ ማሳወቅ አለበት::
- የለውጥ ማስረጃን በወቅቱ ለማያቀርብ የግል ድርጅት ሠራተኛ ወይም ባለመብት ለተተኪው አበል የሚወሰነው ተተኪው አስቀድሞ በአስተዳደሩ ተደራጅቶ በተያዘው መረጃ መሰረት ነው፡፡
- አበል በመቀበል ላይ የሚገኝ ባለመብት የተተኪ ሁኔታን የሚመለከት የመረጃ ለዉጥ ሲያጋጥመዉ ለዉጡ በተከሰተ በ60 ቀናት ዉስጥ ከደጋፊ ማስረጃ ጋር ለአስተዳደሩ በማቅረብ ማሳወቅ አለበት::
- የማህበራዊ ዋስትና የምዝገባ መለያ ቁጥር የተሰጠዉ የግል ድርጅት ሲፈርስ፣ሲከፋፈል ወይም ከሌላ ድርጅት ጋር ሲቀላቀል፡-
ሀ) ስለመፍረሱ፣ የፈረሰዉ ድርጅት ስራ አስኪያጅ ወይም አጣሪዉ
ለ) ስለመከፋፈሉ ወይም ስለመቀላቀሉ ሰራተኞቹን የተረከበዉ የግል ድርጅት ዉሳኔ ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 60 ቀናት ዉስጥ ለአስተዳደሩ በጽሑፍ ማሳወቅ አለበት::
1.5. አደጋን ስለማስታወቅ
- አንድ የግል ድርጅት ሠራተኛ የሥራ ላይ ጉዳት የደረሰበት እንደሆነ የግል ድርጅቱ አደጋው ከደረሰበት ቀን አንስቶ ባሉት ፴ ቀናት ውስጥ በጽሑፍ ለአስተዳደሩ ማስታወቅ አለበት፡፡ ይህ ባለመደረጉ በግል ድርጅት ሠራተኛው ላይ ለሚደርሰው ጉዳት የግል ድርጅቱ ኃላፊ ይሆናል፡፡
አድራሻ፡–
የአስተዳደሩ ዋና መ/ቤት፡- መገናኛ ሕዳሴ ህንፃ ዝቅ ብሎ የቦሌዉ ገርጅ ታክሲ መያዣ ፊት ለፊት፣ ስ.ቁ. 0111550363 ወይም 0111550364 ወይም 0111550368
የዲስትሪክቶች ስ.ቁ. አዲስ አበባ 0118696388፣ ሸገር 0115575454፣ድሬዳዋ 0251111042፣አዳማ 0221110751፣ ባህርዳር 0582262529፣ ኮምቦልቻ 0335513648፣ ነቀምቴ 0576615696፣ ጅማ 0471114352፣ ሀዋሳ 0462216953፣ መቀሌ 0344401290፣
3. የጡረታ አበል ዓይነቶች
3.1. የአገልግሎት እና የጤና ጉድለት ጡረታ አበል
- ቢያንስ 10 አመትያገለገለ የግል ድርጅት ሠራተኛ አገልግሎት ካቋረጠ የጡረታ መውጫ እድሜው ሲደርስ ወይም የጡረታ መውጫ እድሜው ሳይደርስ በጤና ጉድለት ምክንያት ለስራ ብቁ አለመሆኑ በህክምና ከተረጋገጠ ይኸው ከተረጋገጠበት ጊዜ ቀጥሎ ካለው ወር ጀምሮ የአገልግሎት ጡረታ አበል እስከ እድሜ ልኩ ይከፈለዋል፡፡ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየም ካረፈበት ጊዜ ቀጥሎ ካለው ወር ጀምሮ ለተተኪዎች የጡረታ አበል ይከፈላል፡፡
- እድሜው 60 ዓመት ሲሞላ የጡረታ መብት መከበሩ እንደተጠበቀ ሆኖ በዲሲፕሊን ጉድለት ምክንያት አገልግሎቱ ከተቋረጠ ሠራተኛ በስተቀር ቢያንስ 25 አመትና በላይ አገልግሎ እድሜው 55 ዓመትና በላይ ከሞላ በራሱ ፈቃድ አገልግሎቱ ከተቋረጠ የጡረታ እድሜው ሊደርስ 5 አመት ሲቀረውጀምሮ እስከ እድሜ ልኩ የአገልግሎት ጡረታ አበል ይከፈለዋል፡፡
3.2 የአገልግሎትና የጤና ጉድለት ዳረጎት
- ከ10 አመትያነሰ ጊዜ አገልግሎት የፈፀመ የግል ድርጅት ሠራተኛ የጡረታ መውጫ እድሜው በመድረሱ ወይም በጤና ጉድለት ምክንያት ከስራ ሲሰናበት የአገልግሎት ወይም የጤና ጉድለት ዳረጎት ይከፈለዋል፡፡
- የሥራ ላይ ጉዳት ጡረታ አበል
- አንድ የግል ድርጅት ሠራተኛ በሥራ ላይ በሚደርስ ጉዳት ምክንያት ከ ፲ በመቶ ያላነሰ ሊድን የማይችል ጉዳት ደርሶበት ደመወዝ የሚያስገኝ ማናቸውንም ሥራ መሥራት የማይችል በመሆኑ ከሥራ ሲሰናበት የጉዳት ጡረታ አበል እስከ እድሜ ልኩ ይከፈለዋል፡፡
- የጉዳት ዳረጎት
- አንድ የግል ድርጅት ሠራተኛ ከ ፲ በመቶ ያላነሰ ከሥራ የመጣ ጉዳት ደርሶበት ሥራ ለመሥራት የሚችል ከሆነ የጉዳት ዳረጎት ለአንድ ጊዜ ይከፈለዋል፡፡
- የግል ድርጅት ሠራተኛው አግባብ ባለው ሕግ ወይም ኅብረት ስምምነት መሠረት በአሠሪው የጉዳት ካሣ ወይም የመድን ክፍያ የሚያገኝ ከሆነ የጉዳት ዳረጎት አይከፈለውም፡፡
- የተተኪዎች ጡረታ አበልና ዳረጎት
- ማንኛዉም የግል ድርጅት ሰራተኛ፡-
ሀ) የአገልግሎት ወይም የጤና ጉድለት ወይም የጉዳት ጡረታ አበል በመከፈል ላይ እያለ ወይም
ለ) ቢያንስ አስር ዓመት አገልግሎ በስራ ላይ እያለ ” ወይም
ሐ) በስራ ላይ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት ከሞተ ለተተኪዎች የጡረታ አበል ይከፈላል::
የሟች ተተኪዎች የሚባሉት፡-
ሀ) ሚስት ወይም ባል፣
ለ) ከ18 አመት በታች የሆኑ ልጆች ወይም አካል ጉዳተኛ ወይም የአእምሮ ህመምተኛ ልጅ ሲሆን ዕድሜው ከ21 አመት በታች የሆኑ ልጆች፣ ህጋዊ የጉዲፈቻ ልጆችንም ይጨምራል፡፡
ሐ) ልጃቸው ከመሞቱ/ቷ በፊት ሙሉ በሙሉ ወይም በአብዛኛው በሟች ይተዳደሩ የነበሩ ወላጆች ናቸዉ፡፡ ከአስር ዓመት ያነሰ አገልግሎት ያለዉ ሰራተኛ በስራ ላይ እያለ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለየ ለተተኪዎች የአንድ ጊዜ ዳረጎት ይከፈላቸዋል::
3.6 የተተኪዎች ጡረታ አበል መጠን
- ለሟች ሚስት/ ባል የሚከፈለው የጡረታ አበል ሟች ያገኝ/ ሊያገኝ ይችል የነበረው የጡረታ አበል 50በመቶ ይሆናል፡፡
- ነገር ግን አካል ጉዳተኛ ሚስት ወይም ባል ካልሆኑ በስተቀር የሟች ሚስት ወይም ባል የጡረታ አበል በመቀበል ላይ እያለች/እያለ ጋብቻ ከፈጸመች/ከፈፀመ:
- ሚስት እድሜዋ ከ45 አመት በታች ከሆነ ባል እድሜው ከ50 አመት በታች ከሆነ ጋብቻ ከፈጸሙበት ቀን ቀጥሎ ካለዉ ወር ጀምሮ በመከፈል ላይ ያለዉ የጡረታ አበል ይቋረጣል፡፡
- የሟች ልጅ የጡረታ አበል ሟች ያገኝ ወይም ሊያገኝ ይችል የነበረው የጡረታ አበል 20 በመቶ ይሆናል ሁለቱም ወላጆቹ የሞቱበት ልጅ ከእያንዳንዳቸው አበል 20 በመቶ የሚከፈለው ሲሆን የጡረታ አበሉ ድምር ከ30 በመቶ ያነሰ አይሆንም፡፡
- ለሟች ወላጆች የሚከፈለው የጡረታ አበል ሟች ያገኝ የነበረው ወይም ሊያገኝ ይችል የነበረው የጡረታ አበል 15 በመቶ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ከወላጆች ሌላ ተተኪ ከሌለ 20 በመቶ ይሆናል፡፡
- ለሟች ሚስት ወይም ባል ከአንድ በላይ የጡረታ አበል የሚከፈልበት ሁኔታ ሲያጋጥም አንዱና የሚበልጠው ብቻ ይከፈላል፡፡ ካይ የአገልግሎት ዘመን ስሌትን እና የ36 ወራት አማካኝ ደመወዝ አባዝተን ለመቶ ስናካፍል ማለትም 62.7%*16,333.33=ብር 10,240.99 የጡረታ አበል ይሆናል፡፡33.3አአማካይ የአገልግሎት ዘመን ስሌትንዘመን ስሌትን እና የ36 ወራት አማካኝ ደመወዝ አባማለትም 62.7%*16,333.33=ብር 10,240.99 የጡረታ አበል ይሆናብር 10,240.99 የጡረታ አበል ይሆናል፡፡
አድራሻ፡–
የአስተዳደሩ ዋና መ/ቤት፡- መገናኛ ሕዳሴ ህንፃ ዝቅ ብሎ የቦሌዉ ገርጅ ታክሲ መያዣ ፊት ለፊት፣ ስ.ቁ. 0111550363 ወይም 0111550364 ወይም 0111550368
የዲስትሪክቶች ስ.ቁ. አዲስ አበባ 0118696388፣ ሸገር 0115575454፣ ድሬዳዋ 0251111042፣
አዳማ 0221110751፣ ባህርዳር 0582262529፣ ኮምቦልቻ 0335513648፣ ነቀምቴ 0576615696፣ ጅማ 0471114352፣ ሀዋሳ 0462216953፣ መቀሌ 0344401290፣
2.የጡረታ መዋጮ ገቢ እና የአሰሪ ድርጅቱ ግዴታ
- ለግል ድርጅት ሠራተኞች አገልግሎት ጡረታ ፈንድ በሠራተኛው ጥቅል ወርሀዊ ደመወዝ ላይ በመመስረት፡-በግል ድርጅት ሠራተኛው7%፣በግል ድርጅቱ 11% በድምሩ 18% ይሆናል፤
- እያንዳንዱ የግል ድርጅት ለሠራተኞቹ የወር ደመወዝ ከሚከፈልበት ወር መጨረሻ ቀን አንስቶ በ ፴ ቀናት ውስጥ የሠራተኞቹን የጡረታ መዋጮ ከደመወዛቸው በመቀነስ እና የድርጅቱን ድርሻ በመጨመር ለጡረታ ፈንዱ ገቢ የማድረግ ግዴታ ያለበት ሲሆን መዋጮውን ሳይቀንስ የቀረ የግል ድርጅት ክፍያውን ራሱ ለመፈፀም ሀላፊይሆናል፡፡
- መከፈል የሚገባውን የጡረታ መዋጮ በ30 ቀናት ውስጥ ገቢ ያላደረገ የግል ድርጅት ገቢ ባላደረገው የጡረታ መዋጮ ላይ ደመወዝ ከሚከፈልበት ወር ቀጥሎ ካለው ወር የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ በባንክ ማስቀመጫ ወለድ መጠን መሰረት የሚታሰብ ወለድ እና በየወሩ 5 በመቶ ቅጣት ጨምሮ የመክፈል ግዴታ ይኖርበታል፡፡
- በአዋጅ 1268/2014 አንቀፅ 12 ንዑስ አንቀፅ 9 መሰረት አስተዳደሩ ተገቢውን የጡረታ መዋጮ ለጡረታ ፈንዱ ገቢ ሳያደርግ ከሶስት(3) ወር በላይ የቆየን የግል ድርጅት ዕዳ በባንክ ወይም በፋይናንስ ተቋም ካለው ሂሳብ ላይ ተቀንሶ ገቢ እንዲሆን የማስደረግ ሥልጣን አለው፡፡
- በጡረታ ዐቅዱ የተሸፈኑ ሠራተኞችን ቀጥሮ በማሠራት ደመወዝ የሚከፍል አሰሪ ገንዘቡ የሚገኝበትን ባንክና ቅርንጫፍ ከነሂሳብ ቁጥሩ በፅሁፍ የማሳወቅ፣ ለውጥ ሲኖርም ለውጡን ተከታትሎበ15 ቀናት ውስጥ ለአስተዳደሩ የማሳወቅ ግዴታ ያለበት ሲሆን ሂሳቡ የሚገኝበት ባንክም በአስተዳደሩ ወይም ውክልና በተሰጠው አካል ውዝፍ የጡረታ መዋጮ ገቢ እንዲያደርግ ሲጠየቅ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ከግል ድርጅቱ ሂሳብ ላይ ቀንሶ ገቢ የማድረግ ግዴታ አለበት::
- ከጡረታ መዋጮ ገንዘብ ላይ ቀንሶ ለአገልግሎት ክፍያ፣ ለገንዘብ ማስተላለፊያ፣ ለዕዳ ወይም ለማንኛውም አገልግሎት መጠቀም የተከለከለ ሲሆን የጡረታ መዋጮ ክፍያ ከማንኛውም ዕዳ ክፍያ ቅድሚያ ይሰጠዋል፡፡
- በአንቀጽ ፮ ንዑስ-አንቀጽ (፭) መሠረት የፈረሠ፣ የተከፋፈለ ወይም የተቀላቀለ የግል ድርጅት ስራ አስኪያጅ በአዋጁ አንቀፅ ፲፪ ንዑስ አንቀፅ ፲፯ መሰረት ድርጅቱ ለሚፈለግበት ውዝፍ የጡረታ መዋጮ ዕዳ ኃላፊ ይሆናል፡፡
- የሚመለከታቸው አካላት የጡረታ መዋጮ በህጉ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ለአስተዳደሩ በሚወክላቸው አካላት አማካኝነት ተሰብስቦ ለጡረታ ፈንዱ እንዲገባ ከአስተዳደሩ ጋር የመተባበር ግዴታ አለባቸው፡፡
- የባለመብቱ አገልግሎት ዘመንና ማባዣ ቀመር በምሳሌ
1ኛ. ከ1/6/1972ዓ/ም-30/05/2001 ዓ/ም= 29 ዓመት ቢያገለግል
2ኛ. 1/11/2003ዓ/ም-30/12/2010 ዓ/ም = 7ዓመት ከ 2ወር ቢያገለግል
በድምሩ 36 ዓመት ከ2 ወር አገልግሎት ተፈጽሟል፡፡
የመጀመሪያዉ 10 ዓመት = 30%
የቀረዉ 26 ዓመት ሲባዛ 1.25% = 32.5%
ቀሪዉ 2 ወር 2/12 ሲባዛ 1.25% = 0.20%
አማካይ የአገልግሎት ዘመን ስሌት ድምር =62.7% ይሆናል፡፡
- የመጨረሻው 36 ወራት አማካኝ ደመወዝ
ከ1/1/2008—30/08/2009 =20 ወራት ደመወዝ 15,000 ቢሆን 20*15,000=300,000 ይሆናል፣
ከ1/09/2009-30/12/2010 =የ16 ወራት ደመወዝ 18,000 ቢሆን 16*18,000= 288,000 ይሆናል፡፡
ድምር 588,000
588,000/36= 16,333.33
አማካይ የአገልግሎት ዘመን ስሌትን እና የ36 ወራት አማካኝ ደመወዝ አባዝተን ለመቶ ስናካፍል ማለትም አማካይ የአገልግሎት ዘመን ስሌትን እና የ36 ወራት አማካኝ ደመወዝን አባዝተን ለመቶ ስናካፍል ማለትም 62.7*16,333.33/100 ወርሀዊ የጡረታ አበል መጠን ብር 10,240.99 ይሆናል ማለት ነዉይ፡፡ጡረታ አበል ይሆናል፡፡
አድራሻ፡–
የአስተዳደሩ ዋና መ/ቤት፡- መገናኛ ሕዳሴ ህንፃ ዝቅ ብሎ የቦሌዉ ገርጅ ታክሲ መያዣ ፊት ለፊት፣ ስ.ቁ. 0111550363 ወይም 0111550364 ወይም0111550368
የዲስትሪክቶች ስ.ቁ. አዲስ አበባ 0118696388፣ ሸገር 0115575454፣ድሬዳዋ 0251111042፣አዳማ 0221110751፣ ባህርዳር 0582262529፣ ኮምቦልቻ 0335513648፣ ነቀምቴ 0576615696፣ ጅማ 0471114352፣ ሀዋሳ 0462216953፣ መቀሌ 0344401290፣