ሥልጣንና ተግባራት

አስተዳደሩ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-

፩/ በአዋጁ ላይ የተመለከቱትን ሥልጣንና ተግባራት በሥራ ላይ ያውላል፤

፪/ የግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ ዐቅድን ለማስፈጸም ግልጽ ቀልጣፋና ተጠያቂነት
ያለው አሠራር በመዘርጋት ይተገብራል፤ ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤

፫/ እንደ አስፈላጊነቱ የግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ ዐቅድና ፈንድ አስተዳደር
አሠራርን በሚመለከት ጥናት እየተካሄደ ማማሻሻያ ያደርጋል፡፡

፬/ የግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ ዐቅድን ለማስፈጸም ዘመናዊ የሆነ የመረጃ
አያያዝ ሥርዓትን ያደራጃል፤ የአሠራር ሥርዓቱን ያዘምናል፤

፭/ ለጡረታ መብት ብቁ የሚያደርጉ የግል ድርጅት ሠራተኞች ማስረጃዎችን
በቅድሚያ አሰባስቦ አደራጅቶ ይይዛል፤

፮/ የግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ መዋጮ ገቢ አሰባሰብ ሥርዓትን ይዘረጋል፤መዋጮ
ይሰበሰባል፤ በገቢ ሰብሳቢ አካላት በኩል በተገቢው ጊዜና መጠን መሰብሰቡን ያረጋግጣል፤የግል ድርጅቶች ሥርዓቱን ተግባራዊ ማድረጋቸውን
ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፡፡

፯/ የግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ መብትን ለማስከበር የሚቀርቡ ማስረጃዎችን
ብቃትና ተቀባይነት፤የጥቅም አይነት እና መጠኑን ይወስናል፤ክፍያ ይፈጽማል፤የግል ድርጅት ሠራተኞች የጡረታ መብትና ጥቅምን አስመልክቶ
በሚቀርቡ አቤቱታዎች እና ቅሬታዎች ላይ ውሳኔ ይሠጣል፤

፰/ በአዋጁ አንቀጽ ፲፬ መሠረት የግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ ፈንድ ኢንቨስትመንት
ስትራቴጂዎችን ያዘጋጃል፤ለግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ ፈንድ አዋጭና አስተማማኝ የሆኑ የኢንቨስትመንት መስኮችን እና ስብጥሮችን
እያጠና የጡረታ ፈንዱን ኢቨስትመንት  ሥራ ላይ ያውላል፤

፱/ የጡረታ ፈንዱን ገቢና ወጪ ይከታተላል፤ይቆጣጠራል፤ቀጣይነትና አስተማማኝነቱን
ለማረጋገጥ የሚያስችል የአክቹዋሪ ጥናት በማካሄድ የአጭር እና የረዥም ጊዜ ፋይናንሺያል ፕሮጀክሽን እንዲኖር ያደርጋል፤

፲/ የግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ ፈንድንና ከፈንዱ ጋር የተያያዙ ሀብቶችን
ያስተዳድራል፤

፲፩/ በአዋጁ አንቀጽ ፵፭ መሠረት አጠቃላይ የሀገሪቱን ማክሮ ኢኮኖሚና
የጡረታ ፈንዱን ሁኔታ ያገናዘበ ጡረታ አበል መጠንና ማስተካከያ ለማድረግ ለቦርዱ ያቀርባል ሲወሰንም ተግባራዊ ያደርጋል፤

፲፪/ የግል ድርጅት ሠራተኞች ጡረታ ዐቅድና ፈንድን የሚመለከቱ የፖሊሲ
ጉዳዮች ለብሔራዊ ባንክ ያቀርባል፤ የማህበራዊ ዋስትና ስለሚስፋፋበት ሁኔታ መንግስትን ያማክራል፤

፲፫/ የጡረታ ፈንዱን ቀጣይነትና አስተማማኝነት ያረጋግጣል፤

፲፬/ የአስተዳሩን ድርጅታዊ መዋቅራዊ አደረጃጀት፤ የሠራተኞች የደመወዝ
ስኬል፤የአበል እና ልዩ ልዩ ጥቅማጥቅም ይወስናል፤የቅጥር፤የደረጃ እድገትና የዝውውር፤የድልድል፤የሥነ-ምግባር፤ እና ሌሎች የአስተዳደር
መመሪያዎችን ያወጣል፤

፲፭/ አዋጁን እና ይህን ደንብ ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ መመሪያዎችን ያወጣል፤

፲፮/ የንብረት ባለቤት ይሆናል፤ውል ይዋዋላል፤በስሙ ይከሳል፤ይከሰሳል፤

፲፯/ ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚያስፈልጉ እና በሥልጣን እና ተግባሩ
ሥር የሚካተቱ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡



. Powers and Duties of the Administration

The
Administration shall have the powers and duties to;

1/ implements the power and duties provided under the proclamation;

2/ establish transparent, effective and accountable system, monitor and control
the implementation of private Organization Employees’ pension scheme;

 3/  when necessary undertake studies on private
Organization Employees’ pension scheme and fund Administration system and make
amendment accordingly;

4/ in order to implement private organizations employees’ pension scheme, organize
modern data handling system; modernize working system;

5/ collect and organize in advance appropriate evidentiary documents for pension
benefit entitlement of private organization employees;

6/ establish a system for the collection of private organization employee’ pension
contributions, Collect contributions, ensure the pension contributions
collected by the revenue collection bodies in the appropriate time and amount,
supervise and control the implementation of the system by private
organizations;

7/ determine the adequacy and validity of the evidentiary data’s provided for
pension benefit entitlement of the private organization employees’, types and
amounts of benefits, and effect payments, give decisions for the petitions and
claims of pension rights and benefits of private organization employees;

8/ pursuant to Article 14 of the proclamation, prepare private organizations employees’
pension fund investment strategies, undertake  studies on sustainable and reliable investment
sectors and portfolio mix and implement accordingly;

9/ follow-up and oversee pension fund revenue and expenditures, undertake
actuarial study to ensure sustainability and reliability of the pension fund
and prepare long term and short term financial projection;

10/ administer private organizations’ employees’ pension funds and assets related
thereto;

11/ based on the overall macro- economy of the country and the pension fund status
conducts study for pension benefit and amount adjustment and submit to the
Board according to Article 45 of the proclamation and implement the same upon
approval;

12/ submit policy issues related to private organizations employee’s pension scheme
and fund to the National bank of Ethiopia; consult the government on the
extension of social security coverage;

13/ ensure the sustainability and reliability of the pension fund;

14/ decide the administration organizational structure, employee’s salary scale,
allowance and different fringe benefits, and enact recruitment, promotion,
transfer, redeployment, ethics and other administrative Directives.

15/ issue Directives for the implementation of the proclamation and this
Regulation;

16/ own property, enter into contracts, sue and be sued in its own name;

17/ carry out such other activities under its power and duty as may be necessary
for the fulfillment of its objective.